የ 2017 ዓ/ም የካፈቾ ዘመን መለወጫ (ማሽቃሮ ) በዓል በካፋ ዞን ሺሾንዴ ወረዳና ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዉሏል።
ለፓናል ውይይት የተዘጋጀው ሰነድ የሺሾንዴ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተክለዓብ ወ /ገ/ብረዓል ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጓል።
ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት ባህልና እሴት ከንግግር ፣ከፅሑፍና ከቁስ ልገኝ እንደሚቻል ተናግረው ህዝቡ በባህልና እምነት ውስጥ ያለውን ልዩነት አጉልቶ መለየት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ባህል የሰው ልጆች የመተሳሰብ፣ መዋደድና የመፈቃቀር ምልክት እንደሆነ ከግንዛቤ በማስገባት ለትውልድ ማሻገር እንደሚገባ በሰነዱ ተመላክቷል።
ይህንን መልካም እሴት ያለውን የካፋን ባህል ለትውልድ የማውረስ ስራን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ እንደሆነ የሽሾእንደ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተክለዓብ ወ /ገ/ብረዓል ተናግረዋል።
የሺሺንዳ ከተማ አስተዳዳር ከቲባ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ገ/የሱስ በበኩላቸው በዓሉ የአጠቃላይ ካፈቾ የማንነት መገለጫ በዓል በመሆኑ እስካሁን ያለውን አንድነታችንን አጠናክረን ልዩነትን በማጥበብ የጋራ ትግል በማድረግ ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ መቻል አለብን ብለዋል።
ፓናል ውይይቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሽሾእንደ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደምሴ ገ/ማሪያም እንዳሉት በዓሉ ታሪክ፣ቅርስና ባህላችንን ለነገው ትውልድ የማስተላለፉ ስራ ትኩረት ተሰጥተው ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል ።
አስተዳዳሪው አክለሎ በዓሉን አስመልክተው አንዳንድ የግንዛቤ ችግር ያለባቸው ሰዎች ላይም የተለየ የግንዛቤ ስራ ሊሰራ እንደሚገባም ገልጸው ልዩነቶችን በማጥበብ አንድነታችን በማጠናከር የካፈቾ ዘመን መለወጫ በዓልን በዩኒስኮ ማስመዝገብ አለብን ብለዋል።
በማስቀልም ከቲባ ካፊቾ የተለያዩ ታሪኮችና ቅርሶች ባለቤት መሆኗን ለቀጣይ ትውልድ ግንዛቤ በመፍጠር እያወረስን ማክበር እንዳለብንም አሳስቧል::


More Stories
የካፈቾ ብሔር የዘመን መለወጫ (ማሽቃሬ ባሮ) አካል የሆነው የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም በመካሄድ ላይ ይገኛል።