

የካፈቾ ብሔር የዘመን መለወጫ (ማሽቃሮ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች፣ የባህል መሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የነገስታት መናገሻ በኾነውና ከቦንጋ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው “ቦንጌ ሻምበቶ” ተከብሯል።
በክብረ በዓሉ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የማሽቃሮ ዕሴት የኾኑ አብሮነትና አንድነትን በማጠናከር ለልማትና ለኅብረ ብሄራዊ አንድነት ግንባታ ማዋል ይገባል ብለዋል።
የዘንድሮው የማሽቃሮ በዓል የጥንት የካፈቾ ብሔር የስልጣኔና ታሪክ እንዲሁም ባህል መገለጫ የኾኑና ከ128 ዓመታት በፊት ከአከባቢው ተወሰደው የነበሩ የንግሥና ዘውድ እና ዙፋን ለባለቤቱ ህዝብ ለእይታ ክፍት በኾነበት በመኾኑ ልዩ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

More Stories
ተናፋቂው “ማሽቃሮ” በካፋ ንጉሳዊ ስርዓት ታጅበው በድምቀት መከበር ጀምሯል።
mashiqaaro at bonge shambeto
በ ወብሳይታችhttps://kaffaculturetourism.com ይከታተሉ