የካፌቾ፣ ናይ እና የጻራ ብሔረሰቦች የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም በቦንጋ ከተማ በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል።
በሲምፖዚየሙ ከተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢ የተገኙ የብሔረሰቡ ተወላጆችና ምሁራን፣ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎችና ተጋባዥ እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየሙ በካፋ ውስጥ የሚገኙ የካፌቾ፣ የናይ እና የጻራ ብሔረሰቦች ታሪክና ባህል ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፋች በምሁራን ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግም ተመላክቷል።
የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየሙ በዛሬው ዕለት በይፋ በአደባባይ መከበር የሚጀመረው የካፈቾ ብሔር የዘመን መለወጫ (ማሽቃሮ) አካል ነው


More Stories
ማቃሮ አከባበር በከፋ