የካፈቾ ብሔር የባህልና የቋንቋ ሲምፖዚየም በቦንጋ ከተማ ካፋ ባህል አዳራሽ እየተካሄደ ነው

Spread the love

የካፈቾ ብሔር የዘመን መለወጫ የማሽቃሬ ባሮ በዓል አከባበር አካል የሆነው የባህልና የቋንቋ ሲምፖዚየም በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በሲምፖዚየሙ ላይ የካፈቾ፣ ናይና ጻራ ብሔረሰቦች የባህልና ቋንቋ ጥናት እና የማሽቃሬ በዓል አከባበርን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ይደረጋል::

በሲምፖዚየሙ የካፈቾ፣ ናይና ጻራ ብሔረሰብ ተወላጆች፣ ምሁራን እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ሲል ካፋ ቴሌቪዥን ዘግቧል: